|
2009-05-24
መላ መጽሐፍ ቅዱስን
በአውዲዮ (በድምጽ) በአንድ ዲቪዲ እጅግ
መጠነኛ በሆነው ዋጋ (150 የስዊድን ክሮነር/18 ዶላር/ ለኢትዮጵያ ነዋሪዎች 25
ብር) ማግኘትና መገልገል እንደምትችሉ ስንገልጽ በደስታ ነው።
ቅጂዎቹ ኤም. ፒ. ስሪ. (*.mp3) በሚባለው ፎርማት
የተዘጋጁ ናቸው። ከግዢው የሚገኘው አነስተኛ ትርፍ
ለቤተክርስቲያናችን የሕንጻ ስራ አገልግሎት የሚውል እንደሚሆንና በዚህ ግዢ በመሳተፍ ለእግዚአብሔር ስራም አስተዋጽኦ
እያደረጋችሁ እንደሆነ እንድታውቁ እንወዳለን።
መላ መጽሐፍ ቅዱስን በዲቪዲ በፖስታ እንዲላክላችሁ የምትሹ
ወገኖች ሁሉ ሙሉ
አድራሻችሁን ከዚህ በታች እንድታኖሩልን
እንጠይቃለን። በተጨማሪም ትእዛዛችሁን በተመለከተ ኢሜል ስለምንጽፍላችሁ ኢሜላችሁ
በትክክል ማስፈራችሁን እንድትፈትሹ አደራ እንላለን።
ምዝገባ የምታደርጉበትን ተራ ጠብቀን በቅድሚያ ትእዛዝን ላስገባችሁ
በቅድሚያ የመላ መጽሐፍ ቅዱሱን ዲቪዲ ስለምንልክ በተቻላችሁ መጠን ምዝገባችሁን
በቶሎ ብትልኩልን
በቅልጥፍና ትእዛዛችሁን ለማስተናገድ ይረዳናል።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
የኢየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የኢንፎርሜሽን
ቴክኖሎጂ አገልግሎት |