ቀን፤ 2005-11-14  

ስለግብረሰዶም መንፈስ አጠቃለይ ገለጻ ወደተሰጠበት ድረገጽ ለመሄድ እዚህ ይጫኑ

 

አለምን ያነጋገረውና ተከሶ እስከ ስዊድን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረሰው የመጋቢ ኦከ ግሪን ስብከት የአማርኛ ትርጉም

 

 

መጋቢ ኦከ ግሪን   

በ2003-07-20 በቦርይሆልም ቤተክርስቲያን የሰጡት የመጋቢ ኦከ ግሪን መልእክት የቃል በቃል ትርጉም

(ትርጉም፣ ዮሐንስ ዓሥራት / የኢየሩሳሌም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የአይ. ቲ. አግልግሎት)

ሰዶማዊነት ሰው ሲወለድ አብሮት የተፈጠረ ነገር ነው ወይንስ የክፉ መናፍስት በሰዎች ላይ የሚያደርጉት ስራ ውጤት ነው?

ርእሱ አነጋጋሪና አከራካሪ እንደሆነና <<ክርስቲያን>> ተብሎ በሚባለው ሕብረተሰብም እንኳን ሳይቀር አነጋጋሪ መሆን እንደጀመረ አውቃለሁ! ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔር ቃል እራሱ የምለውን ሰጠኝ እንጂ የራሴን አመለካከት  የሚደግፍልኝን ሃሳብ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ቃል አልሄድኩም።

ስለግብረሰዶምነት ባነሳም <<ክርስቲያን ነን>> ስለሚሉ ግብረሰዶሞችም ሁኔታ በተመለከተ አነሳለሁኝ። ይህ ነገር የዘመን ምልክት ነውን? ሰውስ ከዚያ ነጻ መሆን ይችላልን? እነዚህን ነገሮች አነሳለሁ፤ ብዙ ጊዜ ሰአት ብጠብቅም ዛሬ ግን ሰዓት ላሳልፍ እንደምችል አስባለሁ። 

ከመጀመሪያው እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጥሯቸዋል። እስቲ ከዘፍጥረት ጀምረን እንመልከት። በእግዚአብሔር ቃል ላይ የምንቆም መሆናችን አስፈላጊ ነገር ነው። ከዘፍጥረት ምእራፍ አንድ ቁጥር 27-28

27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።

በዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ አባትና እናት ለመሆን እንደተፈርን ያሳያል። <<ወንድና ሴት አድርጎ>> አባትና እናት ሊሆኑ ነው የተፈጠሩትለለ ጌታ በግልጽ ይሄንን ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ ከጋብቻ ውጪ የሆነ ግንኙነት ሁሉ ርኲሰት እንደሆነ ይገልጻል። መጽሐፍ ቅዱስ <<ሴሰኝነት>> በሚለው ቃል ይጠራዋል። በዘፍጥረት 2፣24 ላይ ደግሞ በግልጽ የሚናገረው

     24፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።  

በዚህ ቦታ የሚናገረው ወንድ ከሚስቱ ጋር ስላለው ግንኙነት ነው። ሰው ከሁሉም ጾታ ጋር የኑሮ ወዳጅነት ሊኖረው እንደሚችል የሚገልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ቃል የለም፤ በሌላ መልክም ሊተረጎም የሚችል አባባል የለም።

ሰው ከትዳር ጓደኛው ጋር በታማኝነት እንዲኖርበትና እንዲጠብቅበት እንዲሁም ጥልቅ የሆነ ሕብረትና አንድነትን እንዲለማመድበት እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ያስቀመጠውን ፍላጎትና ተፈጥሮ (በስዊድንኛ ድሪፍት) ሰይጣን እግዚአብሔርንና ትዳርን ለማጥቃት እንደመሳሪያ እየተጠቀመበት ይገኛል። ሰይጣን ይሄንን ፍላጎት አጣሞ ለክፉ አላማ እየተጠቀመበት ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ሰው ተራክቦንና ታማኝነትን፣ ደስታንና በዚያም ውስጥ የሚካተተውን ሁሉ እንዲለማመድ የፈጠረውን ፍላጎት ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ላይ በመወርወር በማጣመምና በማበላሸት እየተጠቀመበት ይገኛል።

በእንስሳት አለም ተባእትና እንስት አለ። እንዲሁም በእጽዋትም አለም ተባእትና እንስት አለ። በእንስሳትም ሆነ በእጽዋት አለም ያልተጠበቀ ባሕርይ የሚያሳይ የለም፤ ነገር ግን ሁሉም ዘር አንዱ ከአንዱ ጋር ሳይቀያየጥ ዘሩን ጠብቆ ሲሄድ እናያለን። የሰው ልጅ በቅርብ አመታት የተለያዩ ዝርያዎችን መቀላቀል እስኪጀምር ድረስ ማለት ነው። ከጽንስ ውስጥ ዘር ማዳቀልና ተመሳሳይ ዝርያን መፍጠር (ክሎኒንግ) እስኪያመጣ ድረስ! የኑሮ ጓደኛን መቀየር በማለት የኑሮ ጓደኛ ሕግም አውጥተዋል።

እንግዲህ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር እንደደነገገው (እንደወሰነው) ስንኖር ቆይተናል ማለት ነው።

የወንድና የወንድን የሴትና የሴትን የኑሮ ጓደኝነትን ሕጋዊ ማድረት ታይቶ የማይታወቅን ቀውጢ (ካታስትሮፊ) ያመጣል።

የዚህን ነገር ውጤት ከአሁኑ በኤድስ በሽታ መስፋፋት በማየት ላይ እንገኛለን። ይሄንን ስንል ኤድስ የያዛቸው ሁሉ ሰዶማውያን ናቸው ማለት አይደለም። ነገር ግን በመጀመሪያ ከግብረሰዶምነት የመነጨ እነደሆነ እናውቃለን። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ከግብረሰዶም ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖራቸውና አንዳችም የሰሩት ክፉ ነገር ሳይኖር በዚህ ክፉ በሽታ ሊያዙ እንደሚችሉ ደግሞ እንመለከታለን።

የሆነው ሆኖ ይህ ነገር ታላቅ ቀውጢን ያመጣል። ከአሁኑ ባለስልጣኖችና የሕብረተሰብ ሹሞች (ሶሻል አደሚኒሰትሬተሮች) ይሄንን ነገር መቆጣጠር ሲሳናቸው ሲቸገሩባቸው ይታያል። ይሄ ብቻ አይደለም ግን ወንዶችና ሴቶች በተለያየ የአባለዘር በሽታዎች እየተለከፉ እንደሆነ ቴሌቪዥን ብዙ አይገልጽልንም። ይህ ሁሉ ሊስፋፋ የበቃው እግዚአብሔር እንደወደደው እየተመላለስን ስለማንገኝ ነው።

ለዚህ ሁሉ መንስኤው የሰው ልጅ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው ውጪ በሆነና ፍጹም ፈር የለቀቀ አኗኗር ስለያዘና ሰው ለሰው ባለው ግንኙነትም ፈር በለቀቀ ኑሮ ስለሚመላለስ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነው አኗኗር <<የግል ሕይወቴ ጉዳይ ነው>> ወይንም <<መብቴ ነው>> የሚባል ጉዳይ አይደለም። ዕብራውያን ምእራፍ 13 ላይ እንዲህ ይላል፤

4 መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።

ሕብረተሰብ በፈለገው አይነት አስተያየት ይሄንን ጉዳይ ቢመለከትም እግዚአብሔር ሕብረተሰብንና የሴሰኝነት ተግባር የሚፈጽሙትን ይፈርድባቸዋል። ይሄንን አስታውሱ (ልብ በሉ)፣ የሴሰኝነት ተግባር የሚፈጽሙትን ሰዎች እንዲሁም ሕብረተሰቡን፣ ከተማውንና ስፍራውን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።

ወደ ዘፍጥረት ምእራፍ 19 ሄደን ብንመለከት ብዙዎቻችሁ ይሄንን አርእስት ዛሬ ስለምናነሳ ይሄንን ክፍል ሳታስቡ አትቀሩም። ይሄንን ጉዳይ በቁጥር 5 ላይ እናገኘዋለን። እዚያም የሚከተለውን እንመለከታለን፣ ከቁጥር አራት ጀምሮ እንየው፤

4፤ ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። 5፤ ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት። በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።

ከወንድጋር ዝሙት ስለሚያደርጉ ወንዶች እዚህ ጋር ለመጀመሪያ ተጠቅሶ እንመለከታለን። በዚህ ስፍራ እንደምንመለከተው የሰዶም ሰዎች ሁሉ ወጣት ሽማግሌ ሳይል ሁሉም ያለሃፍረት ከተፈጥሮ ውጪ ስለሆነ የፍትወት ፍላጎታቸው በግልጽ ሲናገሩና ፍላጎታቸውንም በግልጽ ሲያሳዩ እንመለከታለን። ሽማግሌ አይል ወጣት ሁሉም! ከዚያም እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን <<እናውቃቸው ዘንድ>> ይሄም ግብረስጋዊ ግንኙነት ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግን የግብረስጋ ግንኙነት ለማሳየት የሚጠቀምበት ይሄንኑ አባባል እንደሆነ እንመለከታለን። እንግዲህ ወንዶች ለእርስ በእርሳቸው ምኞትን ሲያሳዩ ይሄው አባባል እዚህም ጋር ተጠቅሶ እናየዋለን።

ነቢዩ ኢሳይያስ ደግሞ እንዲህ ይላል <<9፤…እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ክፉ ነገርን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!>>። የሰዶም ሰዎች ኃጢአታቸውን አይሠውሩም ነበር! ነገር ግን በገሃድ ያሳዩትና በቤቱም ዙሪያ ከበው ጻድቁን ሎጥ ሳይምሩት <<እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።>> ተመኝተናቸዋልና አውጣልን እያሉትነ ነው በአጭር አገላለጽ። በአውራ መንገድ ላይ ቆመው ኃጢአታቸውን ሳይሸሽጉ ምንም ሳያፍሩ በግልጽ ስላላቸው የግብረስጋ ፍላጎት ይናገራሉ። ይሄ ሰዶም ስለነበረችበት ሁኔታ ይገልጻል።

እግዚአብሔር ለአብርሃም በ18ኛው ምእራፍ በ20ኛው ቁጥር ላይ እንዲህ ይለዋል፤

 

20፤ እግዚአብሔርም አለ። የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥

 

<<ኃጢአታቸውም  እጅግ ከብዳለችና>> ይላል። <<የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና>>። ስለዚህ ከመስመር ስለወጣው የግብረስጋ ፍላጎት ያለውን አመለካከት እዚህ ጋር እንመለከታለን፤ <<እጅግ ከብዳለች>>።  እግዚአብሔር ሰዎች በዚህ መልክ ሲመላለሱ ይሄ እጅግ ከባድ ነው ይለዋል።  በግልጽና ባለማፈር ወንዶች እርስ በእርስ ሲሳሳሙ ሴቶችም እንዲሁ እርስ በእርስ ሲሳሳሙ እናያለን። በቴሌቪዥን ፊት ይሄንን ያደርጋሉ። በፊልም ይሄንን ያደርጋሉ። በመንገዶቻችንና በዋነኛ ቦታዎች ይሄንን ማድረግ ብቻ ግን አይደለም፣ ዛሬ በአገራችን ላይ ይሄንን እያደረጉ ይገኛሉ። እግዚአብሔር ስለዚህ ምን ይላል? አዎን እርሱ ይህ ነገር <<እጅግ ከባድ ነው>> ነው የሚለው። በሰዶምና በገሞራ እንዲሁም በእነዚያ ከተሞች እንደነበረ ሁሉ  ይህ ነገር ዛሬም እጅግ ከባድ ነው። 

ጳውሎስ በፊሊጵስዩስ 3፣ 19 ላይ <<ክብራቸው በነውራቸው ነው >> (በስዊድንኛው መጽሐፍ ቅዱስበግብረስጋ ሙከሮቻቸው ይመካሉ” ('de skryter med sina sexuella bedrifter')) ይላል። ዛሬ ሰዎች ሲያደርጉት የምንመለከተው ታዲያ ይሄንኑ አይደለምን?

ሰዎች ዛሬ በእግዚአብሔር የፍጥረት ስርአት ላይ ተቃውሞ ሊያሰሙ ይፈልጋሉ። እግዚአብሔር የሰው ልጅ ትውልዱን ይተካበት ዘንድ ወንድና ሴት አድርጎ ነው የፈጠረው የሚለው አባባል አይፈለግም። የስዊድን ሕግ ይሄንን የማይፈልግ ሆኖአል እንዲሁም የግብረሰዶም እንቅስቃሴ አራማጆች የእግዚአብሔርን የፍጥረት ስርዓት አይወዱትም። በእግዚአብሔር ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙና የፍጥረትን ስርአትም ሲቃወሙ ይታያል። በዚህም ምክንያት ወንድና ወንድ ሴትና ሴትም <<ወዳጅነት>> እንዲመሰርቱ ይፈቅዳሉ። እንዴት እንደዚህ ሊሆን ይችላል? አዎን ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ የመጀመሪያው ምእራፍ ቁጥር 22 ላይ <<ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥>> ብሎ መልሱን ነግሮናል፤ ወደዚህ ክፍል ከትንሽ ጊዜ በኋላ ተመልሼ እመጣለሁኝ።

አስቡት አገራችንን የሚያስተዳድሩና በፓርላማ የሚቀመጡ ደንቆሮዎች ሲሆኑ አስቡት! እስቲ አስቡት መላ መንግስታችን ከዚህ እብደት ጋር ሲተባበርና ይህ የኃጢአት ጎርፍ በምድራችን እንደ ጎርፍ እንዲገባ ሲያደርጉ የእግዚአብሔር ቃል ይሄንን <<ደንቆሮነት ነው!>> ነው የሚለው። ስለዚህም እግዚአብሔር ይሄንን ኃጢአት በተመለከተ በጣም በጣም ከባድ ነገር ነው እንደሚል አምናለሁ።

ይህ የአኗኗር ዘይቤ በመካከላችን ሊመጣ የቻለው ለምንድነው? እንግዲህ ወደ ሮሜ ምእራፍ አንድ ሄደን ጳውሎስ ይሄንን ርእስ በተመለከተ በስፋት የገለጸውን እንመልከት። ጳውሎስ ግብረሰዶምነት በተመለከተ በስፋት ያነሳበት ምክንያት በሮም መንግስት የግብረሰዶማዊነት አስተሳሰብ እጅግ ተስፋፍቶ ስለነበረ ነው። በዚያን ጊዜ ይህ አስተሳሰብ እጅግ እንዲለመልም ያደረገ ምክንያት ስለነበረና ይሄ አኗኗር በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንም ውስጥ አሻራውን እንዳይጥል ጳውሎስ ይሄንን በተመለከተ በደንብ ትኩረት ሰጥቶ ማስተማር አስፈልጎታል።  ሮሜ ምእራፍ 1 ቁጥር 21፤

20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። 22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ 23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። 24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ 25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። 26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ 27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። 28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤

ታላቁንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታ እግዚአብሔርን ከሁሉ በሚያንስ ታናሽ በሚባለው ነገር ለወጡ። በዚህ ቦታ ላይ ጳውሎስ ሲናገር እንዲህ የሚያደርግ ፍጹም ማስተዋል የራቀው (ደንቆሮ) ሰው ብቻ ነው ይላል። በረከት የሆነውን እግዚአብሔርን አውጥተው ጥለዋል፣ ብቻውን የሆነውን ጌታና የሁሉ ገዢ የሆነውን እርሱን አውጥተው ጥለዋል። የእግዚአብሔር ቃል ሕገመንግስታችንን የእውነት መለኪያችን ነው። የእግዚአብሔርን ቃል እንደ የእግዚአብሔር ቃልነቱ ማመን ነገር ግን በተግባር መካድ ምንም አይጠቅመንም። የእግዚአብሔርን ቃል በአፌ ብናገር በአኗኗሬና በተግባሬ ግን ቃሉን ፍጹም የሚቃረነውን ነገር ባደርግ ምን ዋጋ አለው? የእግዚአብሔር ቃል እንድንታዘዘው ያዘናልና። የእግዚአብሔር ልጆች ነን ብለን እራሳችንን እንድንቆጥርና የእግዚአብሔር በረከት እንዲበዛልን እንዲሁም እግዚአብሔርን እንድናስደስት ከፈለግን የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ ይገባናል።

በቁጥር 28 ላይ፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይላል። የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ የተሰጠው እንደመሆኑ የአሮጌውን ሰው ዝንባሌን ወይ ሊቋቋመው ወይ ደግሞ ሊገዛለት ይችላል። ስልጣኑ ያለው በእጃችን ነው። የሰው ግብረገብአዊ ተፈጥሮ ክፉና ደጉን የሚያሳውቅ ሕግ በውስጣችን ተጽፎ እንደሚገኝ ያሳየናል። የልባችን ውስጥ ያለው የሕሊናችን ድምጽ ሃሳባችን ሲመሰክርብንና ሲከሰን የራሳችን ፈራጅ ሆኖ እናገኘዋለን።

በአንደበታችን <<ይሄ ምንም ችግር የለውም፣ ይሄንን ነገር እኔ አደርገዋለሁ>> ብንል ልባችን ግን ሌላ ነገር ይናገራል። በአንደበትህ እራስህን መከላከልህና ምክንያት ማቅረብህ ምንም አይፈይድም ምክንያቱም ልብህ ይፈርድብሃልና። ልብህ ፈራጅህ ሆኖ በሃሳብህ ላይ ይፈርዳልና። በአንደበታችን ብዙ ልንል እንችላለን ነገር ግን ልባችን ይፈርድብናል ብሎ ከዚህ በታች የተገለጸው ጥቅስ በትክክል ያስረዳናል።

በሮሜ ምእራፍ 2 ቁጥር 14 ጳውሎስ ይሄንን በተመለከተ ሲናገር <<14 ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ 15 እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። >> ስለዚህ ሕሊና አለ። ለእግዚብሔር ጀርባችንን ስንሰጥና የእርሱን እውቀት ለመቀበል እምቢ ስንል እርሱ መንፈሱን ከሕሊናችን ዘወር ያደርጋል። ሕሊናም በዚህ ጊዜ ምንም የማይሰማውና ወደየትም የሚለመጥ ይሆናል። ያን ጊዜ ሰውን ይሄንንና ያንን እንዳያደርግ የሚያግደው ነገር አይኖርም። እግዚአብሔር እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ከዚያ በኋላ አይቆጣጠራቸውምና ወደከፋ ርኲሰት አልፈው ይሰጣሉ።

በቁጥር 24 እንዲህ ይላል፤

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤

ግብረሰዶምነት የሚጀምረው በልብ ፍትወትና ምኞት ነው። ይሄ ነው የሚሆነው። የአይምሮ የሚያሰላስሉት ኃጢአትና የፍትወት ሕልም በውስጣቸው ይመላለሳል። በዚህ ረገድ የብልግናና ነውርን የሚያስፋፋው ኢንዱስትሪ፣ ቴሌቪዥንና የፊልም ኢንዱስትሪ፣ የጋዜጣና መጽሔት ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ፍላጎትን ቀስቅሰው ፈትተው በመልቀቅ አስተዋጽኦአቸውን አበርክተዋል። ይሄንን በማድረግና ለመላው የስዊድን ሕዝብ በግልጽ በማሳየት ዛሬ በቴሌቪዥናችን ላይ ማንኛውንም አይነት ነገር ያሳያሉ። ያለምንም መሸማቀቅ ወይንም ይሄንን ነገር ለማየት የማይፈልጉ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ምንም ማሰብ በማያስፈልጋቸው ሁኔታ በድፍረት ይሄንን ያሳያሉ። ይህ ነገር ሰዎችን ለክፉ ሊጋብዝና ሌሎችን ለመድፈር ሊያበቃ እንደሚችል ቢያውቁም አደገኛም እንደሆነ ቢያውቁም ምንም አይነት እገዳ በዚህ ላይ አያደርጉም።

በግልጽ በስቶክሆልም ጎዳናዎች የሚካሄደውን የግብረሰዶሞችን ሰልፍና መፈክር አውጥተው ያሳያሉ። በአላንድስብላደት (የደቡብ ስዊድን ጋዜጣ ነው) ስለዚህ ጉዳይ አንድ ጽሑፍ ለመጻፍ ዝግጁ እንደሆንኩኝ ገልጬ ነበር። ማንም ግን እንፈልግሃለን ያለኝ አልተገኘም። ስለዚህ ጉዳይ አስተምራለሁ ብዬም ባሮሜትር የተባሉትን ጋብዤ ነበር ግን አንዳቸውም መልስ አልሰጡኝም። ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያም ደውዬ የፊታችን እሁድ በዚህ አንገብጋቢ ርእስ ላይ ላስተምር ስለማስብ መገኘት ትችላላችሁ ብዬ ጋበዝኳቸው። የደወልኩለትና ያነጋገርኩት ሰው <<እሺ ጊዜ አለን እናስብበታለን>> አለኝ። ሰኞ እለት ባናግራቸውም እስከዛሬ ማንም መልስ አልሰጠኝም። ይሄንን ሁኔታ ሊጋፈጥ ዝግጁ የሆነ የለም - እንዲሁ ሊያሳልፉት ብቻ ነው የሚፈልጉት። ኢንገገርድ እንደነገረቺኝ እዚህ ቦርይሆልምም ግብረሰዶማውያን ከሁለት ቀን በኋላ ሰልፍ ለማድረግ እያቀዱ ነው። እንደዚህ አይነቱ ነገር ይታቀዳል፣ ስፍራም ያገኛል። እኛ ግን ያንን የተቃረነ ነገር እንድናቀርብ አይፈለግም። ግብረሰዶምን የተቃረነ ነገር አይፈለግም። የሚፈለገው ግን ብዙሃኑን ተከትሎ መፍሰስ ብቻ ነው።

ሮሜ 1፣26 እንዲህ ይላል

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ 27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤…

የልብ ክፉ ፍላጎት ወደ ነውረኛ ምኞት ተለወጠ። ተቃጠሉ የሚለው ቃል <<መጫር>> ማለት ነው። ሰዎች የሚያደርጉት ይሄንን ነው። በውስጣቸው ያለውን ፍላጎትን ይጭራሉ። የፍትወት ሃሳቦችን በማሰብ፣ ሕልሞችን በማለም፣ ወይንም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በመመልከት በጋዜጦችንና በፊልሞችን በመመልከት እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ ራስን መለኮስ ማለት ነው። ስለዚህ ሰው እግዚአብሔርን በመናቁ ሊያጠፋው የማይችለውን እሳትና ፍላጎት በገዛ እራሱ ላይ ይጭራል።  የሚያሳፍሩት ምኞቶች በሰው ውስጥ ስፍራ አግኝተው ሲቀመጡ እንደእሳት ሊቆጣጠሩትና ሊያጠፉት እንደማይችሉት ሃይል ሆነው ይቀመጣሉ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ እንደሚገልጽልን ሰው አውቆ በራሱ ላይ የሚለኩሰውን የፍትወት መቃጠል እግዚአብሔርም አያጠፋውም። ስለዚህም በቁጥር 27 ላይ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። ይላል።

ስለዚህ ሰዎች ያለምንም ገደብና ቁጥጥር ለግብረሰዶምነት ሲሰጡ እግዚአብሔር በፍትወት እንዲቃጠሉ ይተዋቸዋል። ነገር ግን በዚህ ምኞት በሚቃጠሉ ላይ የፍርድ ቀን ይመጣል ፍርድም ይጠብቃቸዋል።

ጳውሎስ በመልእክቱ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በዚህ አንድ አይነት ሁኔታ እንደነበራቸውና አንዳቸው ከሌላው በዚህ ነገር የተሻሉ እንዳልነበሩ በአጽንኦት ይገልጻል። በሮም መንግስት ጊዜ እንደዚህ ነበረ።

በዘሌዋውያን ምእራፍ 18፣ ላይ እግዚአብሔር ለዚህ ነገር ያለውን አመለካከት የበለጠ ግልጽ የሚያደርጉ ጥቂት ቁጥሮች አሉ። ቁጥር 22

22፤ ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና።23፤ እንዳትረክስባትም ከእንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና።

ይላል የእግዚአብሔር ቃል በዚህ ቦታ።

እስከ ቁ 30 ድረስ ማንበብ እንችላለን…ከቁጥር 27 ጀምረን እናንብብ

27፤ ከእናንተ በፊት የነበሩ የአገሩ ልጆች ይህን ርኵሰት ሁሉ ሠርተዋልና፥ ምድሪቱም ረክሳለችና፤ 28፤ ባረከሳችኋት ጊዜ ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እናንተን እንዳትተፋችሁ። 29፤ ከዚህ ርኵሰት ሁሉ ማናቸውን የሚያደርግ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና። 30፤ ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ቦታ ከተፈጥሮ ውጪ ስለሆኑ ስለነዚህ ነገሮች ያነሳል ያስተምረናልም። ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ከፍትወት ፍላጎት ጋር የተገናኙ ልምምዶች በሕብረተሰብ ውስጥ እንደካንሰር እብጠት ናቸው። በፍትወት ፍላጎት ፈር የለቀቁ ሰዎች እንስሳትን እንኳን እንደሚደፍሩ እግዚአብሔር ያውቃል። የሰዎች ልጆች የፍትወት ፍላጎትና መቃጠል እንስሳትን እንኳን አይምርም።

በቀይ መስቀል ድርጅት ውስጥ ችግር የገጠማቸውን ሰዎች አዳማጭ ሆኜ ለብዙ አመት ሰርቻለሁ።በዚያም አንዳንዶች ከእንስሳት ጋር ስላሳለፉትና ስለረኩባቸው ግንኙነቶች አጫውተውኛል። ስለዚህ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ እንዲሰፍር ያደረገው ነገር እንዲሁ ተረት ያልሆነ ሰዎችም እንዲያስቡበት የወደደው ነገር ነው። እግዚአብሔር በቃሉ ይህ እንዲሰፍር ያደረገው ሰዎች እግዚአብሔርን ትተው በሄዱ ጊዜ እነዚህን ነገሮች እንደሚያደርጉ ስለሚያውቅ ነው።

በነዚህ ኃጢአቶች ምክንያት ምድሪቱ የሚኖሩባትን ሰዎች ትተፋቸዋልች። ዛሬ ለዚህ ነገር በአገራችን ያሉ ፖለቲከኞች ምላሽ ልክ ጳውሎስ በመልእክቱ እንደሚገልጸው ነው። <<እንዲህ ለሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል>> የሚለውንና እግዚአብሔር የወሰነውና የደነገገውን ቃል ያውቃሉ ። ሆኖም አኗኗራቸው ልክ እንደነዚህ ሰዎች ነው፣ ከዚያም የከፋ ነገር ያደርጋሉ። ሰዎች ይሄንን ቢያደርጉት መልካም ነው ባይ ናቸው። የፖለቲከኞች ምላሽ ዛሬም ግፉበት፣ ቀጥሉበት የሚል አጽንኦትን ነው የምናየው። ሰዎች ይሄንን ቢለማመዱ ምንም አይደለም ሊያደርጉት ይችላሉ ባይ ናቸው። አገራችን ግን በታላቅ ቀውጢ ልትጠቃ አደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳለች አረጋግጥላችኋለሁ። እግዚአብሔር <<ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ… ተፋች…>> እንዳለ ከእስራኤል ልጆች በፊት በምድሪቱ የነበሩት ሰዎች በኖሩበት ሁኔታ ከኖሩ ምድሪቱ እንደምትተፋቸው ተናገረ።

የእስራኤል ልጆች ምድሪቱን ሲወርሱ፣ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች እንዳደረጉት አይነት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የተቃረነን ነገር ካደረጉ እንዲህ ይላቸዋል <<ባረከሳችኋት ጊዜ ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እናንተን እንዳትተፋችሁ።>> ይህ ሁኔታ ስዊድን ላይ ሊደርስ እንደሚችል አምናለሁ። በአገራችን ላይ ይሄ በደንብ አድርጎ ሊደርስ ይችላል ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር የተናገረውን ጭራሽ ባለማሰብ አንዳንድ ሕጎችን እንኳን እስከማውጣት ደርሰናልና። አገራችን በቀውጢ አፋፍ ላይ ትገኛለች። የምድር መንቀጥቀጥ በአንድ ጊዜ ተነስቶ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ ሊሞቱ የማይችሉበት ምን ምክንያት አለ? ታላቅ ነፋስ ተነስቶ ብዙ ሺህ ሰዎች በውሃ መጥለቅለቅ አገራችንን ሊመቱ አይችሉም ያለ ማን ነው? ሌሎችስ ቀውጢዎች በስካንዲኔቪያ ላይ የማይደርሱበት ምን ምክንያት አለ?

ሃሰተኛ ዋስትና ውስጥ እንገኛለን። ለራሳችንም <<አይ፣ እኛን እንኳን አይነካንም! ወደ ታች ወደ አውሮጳና በሌሎች ክፍለአለማት ወይንም በቻይና ቢሆን ነው እንዲህ አይነት ነገር የሚከሰተው>> ብለን እናስባለን። እግዚአብሔር እርሱን ስለተውን ነገር ተገለባብጦ እነዚህን ክፉ ነገሮች እንዲያገኙንና ምድሪቱም እንድትተፋን ማድረግ ይችላል።

በጣም እኮ ነው የሚገርመው! አስቡት 300 የማይሞሉ በሕዝብ የተመረጡ ሰዎች እነዚህን ሕጎች ሲያወጡና ሰዎች እንደፈለጉት እንዲኖሩ በመተው አገራችንን ወደ ታላቅ ቀውጢ አፋፍ ሲያደርሱት!!! ያወጡአቸው ሕጎች ምን አይነት ነገር ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ዛሬ ማስተዋል አልቻሉም። ታሪክ ግን ወደፊት ይሄንን ያሳያል።

ልጅ ደፋሪዎች፣ ከገዛ ቤተሰቦቻቸው ጋር ነውር የሚፈጽሙ ወ.ዘ.ተ የሚባሉ አንዳንድ እንግዳ ቃላትን እንድናውቅ ሆነናል። እነዚህ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ልምምዶች ናቸው። በዚህ ጊዜ ወደ 1ኛ ቆሮንቶስ ምእራፍ 6 ሄጄ ሃዋሪያው ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያንን አኗኗር በተመለከተ የሚያነሳውን እንመለከት። በቁ. 9 ላይ እንዲህ ይላል

9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

<<ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሰሩ>> ይላል። እግዚአብሔር አስቀድሞ ሊሆን ያለውን የሚያውቅ ጌታ ነው። ዛሬም ይሄንን እንመለከታለን እያነውም ነው። እንዴት ሊሆን ይችላል? እንላለን። ጳውሎስ በ1ጢሞ 1፣10 ላይ <<ከወንድ ጋር ለሚተኙ>> ብሎ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ቋንቋ <<ለአቅም አዳም ካልደረሰ ወንድ ጋር የሚተኛ>> ይለዋል። እነዚህን መጽሐፍ ቅዱስ ርኲሳን ብሎ ይጠራቸዋል።

በዚህ ጊዜ በአጽንዖት ልናገር የምወደው ነገር ቢኖር ግብረሰዶሞች በሙሉ ለአቅም አዳም ካልደረሰ ወንድ ጋር ይተኛሉ (ፔዶፊል ናቸው) ወይንም ርኲሳን ናቸው እያልኩኝ አይደለም። ሆኖም እንዲህ ያለውን ነገር የሚለማመዱ ሰዎች ወደተከለከሉ አካባቢዎች የሚወስደውን በር በመክፈት ኃጢአት በአይምሮአቸው ውስጥ ምሽግን እንዲገነባ ይፈቅዳሉ።

ዛሬ ሕጻናትን በመድፈር ሕይወት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ከመጀመሪያው እንዲሁ የነበሩ ሰዎች ሳይሆኑ ከእለታት አንድ ቀን ለየት ካለ ሰው ጋር ፍትወትን በመለማመድ ነው ቀስ በቀስ አሁን ወዳሉበት ደረጃ የደረሱት። እንዲህ እያለ ነው የጀመረው።

በግብረሰዶም ግንኙነት ለጓደኛው ታማኝ መሆን (አንድ ፓርትነር ይዞ መቆየት)፣ በየቀኑ ጓደኛን ከመለዋወጥ የተሻለ ነገር አይደለም። ምንም የተሻለ ግንኙነት አይደለም። ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጸያፍ ነገሮች ናቸውና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው። የኑሮ ባልንጀራ አስር ጊዜ መቀያየርና በግብረሰዶም ግንኙነት ውስጥ መገኘት ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት የሆኑ ልምምዶች ናቸው። ምንም ልዩነት የላቸውም።

ግብረሰዶምነት ታዲያ ሰው ሲወለድ አብሮት የተፈጠረ ነገር ነውን?  ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 15ኛ ምእራፍ ቁ. 18 ምን ይላል፤ 

18 ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።

19 ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።

ጌታ ኢየሱስ በግልጽ በዚህ ቦታ ላይ በማያሻማ ሁኔታ ስለ ልብና ስለማይታየው የሃሳብ አለም ያነሳል። ጌታ ኢየሱስ የሚያተኩረው በሃሳብ ላይ ነው። ጌታ ኢየሱስ የምኞት ኃጢአት መነሻቸው በሃሳባችን ውስጥ እንደሆነ ይገልጻል።

ቁጭ ብዬ በሌሊት ሰዎችን አዳምጥ በነበረ ጊዜ ብዙዎችን አነጋግር ነበረ። እያንዳንዳቸውን ወደግብረሰዶምነት ሃሳብ እነዴት እንደመጡ ሲገልጹ በሃሳባቸው ውስጥ ይሄንን በማሰላሰል እንደሆነ ይናገራሉ። ብዙ ጊዜ በወጣትነታቸው ጊዜ ነው ይሄንን አይነት ሃሳብ ለማሰብ የሚበቁት። ሌሎች ደግሞ በትዳራቸው ደስተኛ ሳይሆኑ ሲቀር ሴቶች ሌሎች ሴቶችን ሲሹ፣ ወንዶችም ደግሞ ሌሎች ወንዶችን ይሻሉ። ሁሉም፤ እገሌ ከእገሌ ሳይሉ እነዚህን ነገሮች በሃሳባቸው በማሰላሰል ነው ወደግብረሰዶምነት የገቡት።

ሁሉም ታዲያ መጀመሪያ ላይ ሲሞክሩት የሆነ የሚያቆማቸው ነገር እንደነበረ ይገልጻሉ። አንዴ ተግባሩን ከፈጸሙት በኋላ ግን ያቆማቸው (ያግዳቸው) የነበረው ነገር ይሰበራል።

እንግዲህ እንደምንመለከተው፣ ሰዎች ምንም ሴሰኞች ቢሆኑ እግዚአብሔር አንድ የመጨረሻ መከላከያ እድል ይሰጣቸዋል። <<አንዴ ለመጨረሻ ጊዜ አስብበት>> እንደሚባሉ ያህል ነው። ምናልባት እነዚህ ሰዎች አስበውበታል ነገር ግን የሚመልሳቸውን ድምጽ ተላልፈው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ግን ባደረጉት ጊዜ ሁሉ እየቀለላቸው ሄዷል። ይሄንን ስንመለከት ጌታ ኢየሱስ በሰው ልብና ሃሳብ ውስጥ ስለሚፈጠሩ ኃጢአቶች የተናገረው ይገባናል።

<<ወንዶችም ሴቶችም ከፍጥረታቸው የሚገባውን ለፍጥረታቸው በማይገባው ለወጡ>> ይላል ጳውሎስ በሮሜ ምእራፍ 1። ይህ ማለት ምርጫ አላቸው ማለት ነው። <<ለወጡ>> ማለት አንድን የነበረን ነገር አውጥቶ ሌላን ማስገባት ማለት ነው። ይህ ነፃ ምርጫ ነው። ማንም ያስገደዳቸው አልነበረም። መለወጥ ማለት አንድን ነገር በፈቃደኝነት ማስረከብና ሌላን ነገር በፈቃደኝነት መውሰድ ማለት ነው።

ንጽህናን በፈቃደኝነት አውጥቼ ርኲሰትን እቀበላለሁ ማለት ነው። <<እያወቁ ለወጡ>> ይላል ጳውሎስ።

ግብረሰዶምነት በሽተኛ ነገር ነው። ንጹህ የሆነውን አንድን ሃሳብ ወስዶ በሽታ ባጠቃው ሃሳብ መተካት ማለት ነው። ጤነኛ የነበረው ልብ በሽተኛ በሆነ ልብ ተተካ እንደ ማለት ነው።

ይሄንን ነው ሰዎች ያደረጉት። ጤነኛ የነበረው ሰውነት በተካሄደው ልውውጥ ምክንያት ጠፍቶአል ይላል ጳውሎስ።

ሃዋሪያው ጳውሎስ በ 1ኛ ቆሮ 6፣18 እንዲህ ይላል፤ 18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። ዝሙት ሰውነትን ያዋርዳል። ከዝሙት እንሸሻለን እንጂ ስለዝሙት ውይይት አናደርግም ወይንም ከዝሙት ጋር ውጊያን አናካሂድም። ልክ ዮሴፍ እንዳደረገው። እርሱ ሸሸ። ሎጥን እግዚአብሔርን ምን አለው። <<ነፍስህን ለማዳን ሽሽ!>>። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚለን ሽሹ ነው።

ግብረሰዶምነት ሰው በፈቃዱ የሚመርጠው ነገር ነው ወይ? መልሱ፤ አዎን። ሰው በፈቃዱ መርጦ የሚገባበት ነገር እንጂ ስንፈጠር እንደዚያ ሆነን አልተፈጠርንም። ሰው የሚመርጠው ነገርና ተፈጥሮአዊውን ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ለውጦ የሚገባበት ነገር ነው። በእርግጥ እንዲህ ነው! ይህ ባይሆን ኖሮ ለሰዎች ልጆች ታላቅ ማታለል ተደርጎብናል ማለት ይሆን ነበረ።

ነገሩ ግን ሰው በፈቃደኝነት የሚገባበት ነገር ነው።

ሰው ታዲያ ግብረሰዶምነትን እየተለማመደ ክርስቲያን መሆን ይችላልን?  ከኤፌሶን 5፣ ጥቂት ቁጥሮችን በመመልከት አንዳንድ እውነቶችን ከዚያ እንመልከት። ቁ. 3 እንዲይ ይላል፤

3 ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤

ከዚያም በቁጥር 5 ላይ እንዲህ ይላል፤ 5 ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም። 6 ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።

<<ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ!>> ይላልና ክርስቲያን ሆኜ ግብረሰዶም መሆን እችላለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነ እራስህን ታታልላለህ፣ እራስህንም ታሞኛለህ። አንዳንዶች <<ምንም አይደለም>>፣ <<እግዚአብሔር እኮ ፍቅር ነው>> ወ.ዘ.ተ. ቢሉህ በእርግጥ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ነገር ግን እርሱ ቅዱስ አምላክም ነው። ይሄንን ነገር ደግሞ እጠላዋለሁ ብሎአል። ስለዚህ ግብረሰዶም ሆኖ ክርስቲያን መሆን አይቻልም ማለት ነው። በዚህ ሁኔታ የሚመላለስ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም ሊሆንም አይችልም። ይህ ሰዎች ሁሉ እየሰሙት ልንለው የሚገባን ነገር ነው!  <<ሰዎች ሆይ እራሳችሁን አታታልሉ>>። ከፍተኛ ማጭበርበር እየተካሄደ ነው!! ሰይጣን <<ጥሩ ክርስቲያን ሆነህ በግብረሰዶምነት መኖር ትችላለህ! በግብረሰዶምነት ግንኙነትም ለባልደረባህ ታማኝ ሆነህ መኖር ትችላለህ>> እያለ የሚዋሸው የነፍሳችሁ ጠላት እራሱ ነው!! የእግዚአብሔር ቃል ግን የሚናገረው ሌላ ነው፤ <<ለስሕተት የሚገባ ብድራት (ቅጣት)>> አለ!!

************************************************************************

ከዚህ በኋላ ያለውን የስብከቱን ክፍል አቃቢ ሕጉ በመጀመሪያው ፍርድ ቤት ላይ (ቲንግስሬት) አላቀረበውም። ለምን እንዳላቀረበው ሲገልጽ <<ክሩ በደንብ ስለማይሰማ ነው>> ወ.ዘ.ተ ብሎ ነው ምክንያት የሰጠው። ሆኖም <<በግብረሰዶማውያን ላይ ጥላቻ አነሳስተዋል>> በማለት ለመሰረተው ክሱ የማይመች ስለሆነ ይሆንን? መጋቢ ኦከ ግሪን ባቀረቡት መልእክት ውስጥ ግን ከዚህ በታች የሰፈረው መልእክት አብሮ ነበረበት!

************************************************************************

 

ራእይ 22፤14-15 <<14 ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው። 15 ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።>>

ከዚህ በበለጠ እንዴት ግልጽ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል? በዚህ ሁኔታ ሰው ከተመላለሰ የሚኖረው በውሸት አለም ነውና ወደ እግዚአብሔር መንግስት አይገባም። <<ግብረሰዶም ብሆንም እኔ ክርስቲያን ነኝ>> ብሎ የሚል ቢኖር በዚህ አባባሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት አይችልም። የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረው ይሄንን እንደሆነ ጫን ብዬ ላሰምርበት እፈልጋለሁ!

ስለዚህ ወንድ ወይንም ሴት ክርስቲያን ሆኖ ግብረሰዶም መሆን ይችላልን? ለሚለው ጥያቄ መልሱ፤ <<ፈጽሞ አይቻልም>> ነው። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚል እራስን ማታለል ነው። አንድ ቀንም እንደነዚህ ያሉትን ሃፍረት ይከድናቸዋል።

ይህ ሴሰኝነት የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውን? ሉቃስ 17፣28

አዎን ጌታ ኢየሱስ በሉቃስ ም. 17 ላይ ስለመጨረሻው ዘመን ሲናገር በኖህ ዘመን እንደነበረ የሰው ልጅ በሚመጣ ጊዜ እንዲሁ ይሆናል ካለ በኋላ በሎጥ ዘመን ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ይሸጥና ይለውጥ ነበር። ሎጥ ከሰዶም ከተማ በወጣ ቀን ግን እሳትና ዲን ዘንቦ ሁሉን አጠፋ። የሰው ልጅ በሚመጣም ጊዜም እንዲሁ ይሆናል ይላል።

እነዚህ ከተሞች እንዲሰምጡ፣ እንዲዋረዱና ከምድረገጽ እንዲጠፉ ያደረገው ምን ነበር?

ምክንያቱ ሰዎች በግብረሰዶምነት ይኖሩ ስለነበረ ነው። ስለዚህ በሎጥ ዘመን ሰዎች በግብረሰዶምነት ይኖሩ እንደነበረ ጌታ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ባለው ዘመን ሰዎች እንደገና እንደዚህ ባለ ሁኔታ መኖር ይጀምራሉ። ይህ እንግዲህ የመጨረሻው ዘመን አንዱ ምልክት ነው! ይሄ ምንም ልናስተባብለው የማንችለው ነገር ነው።

ጌታ ኢየሱስ የሰዶም የሕይወት ዘይቤ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በምድር ሁሉ የተስፋፋ እንደሚሆን ገልጾልናል። በዚህ የሕይወት ዘይቤ ዛሬ የሚመላለስ ሰው የእግዚአብሔርን የፍጥረት ስርዓት በመጻረር ይመላለሳል። በማቴ 18 ቁ. 6 ላይ ስለሕጻናት ጌታ ኢየሱስ በሚናገርበት ጊዜ  <<ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።>>

በዚህ ቦታ ላይ <<ማሰናከል>> ብሎ የተተረጎመው ቃል የመጣው ጉድ/ግፍ (ስካንዳል) ከሚለው ቃል ነው። ሕጻናት እንዲህ ላለ ስቃይ መዳረግ ትልቅ ግፍ ነው! ስለዚህ አሁን በግብረሰዶም ግንኙነት ውስጥ በሚያድጉ ሕጻናት ሁኔታ ላይ አተኲራለሁ።

አንድ ሕጻን ልጅ፣ በአባትና በእናት ስር ሊያድግ ሲገባ፣ ይሄንን መንፈግ ግፍ (ስካንዳል) ነው። ጌታ ኢየሱስ ይህ ግፍ ነው ይላል! ምንም የማያውቁ ሕጻናት ለእንደዚህ አይነት ስቃይ መዳረጋቸው የግፍ

ግፍ ነው! ሕጻናትን ከአባትና ከእናት ነጥቆ ለሁለት ወንዶች ወይንም ለሁለት ሴቶች መዳረግ በሕጻናት ላይ ትልቅ ጭከና ነው።

<<ሁለት ወንዶች ወይንም ሁለት ሴቶች ከሌላው እኩል ማሳደግ ይችላሉ>> ቢባል ይህ ከተፈጥሮ ውጪ ስለሆነ ግፍ/ጉድ ነው። ሕጻናት በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እንዲያድጉ መገደዳቸው ግፍ ነው።

ሰዶም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማስጠንቀቂያነት ከ30 ጊዜ በላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። እነዚህ የኃጢአት አስተሳሰቦች በጣም ጠልቀው ስለሰረጹ መቅሰፍቶችም እነዚህን ኃጢአቶች ሊያስተዉ አልቻሉም። ራእ. 9፤20 <<20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤ 21 ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም። >> 

መቅሰፍቶችም ሰዎች ኃጢአታቸውን እንዲተዉ ሊያደርጉአቸው አይችሉም። ይህ ነገር የእርኲሳን መናፍስት እስራት አይደለምን? በሰው ውስጥ እጅግ ጠልቆ ያለ ነገር ስለሆነ መቅሰፍቶች ሲመጡ ሴሰኞች ምግባራቸውን አያቆሙም ነገር ግን እንደለመዱት በሴሰኝነት ይቀጥላሉ።

ስለዚህ በርኲሳን መናፍስት መያዝ ማለት ነው። መልካም የጋብቻ ሕይወት ከሴሰኝነት ኃጢአት ይጠብቃል። 1ቆሮ 7፣2-5 <<2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት። 3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። 4 ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። 5 ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።>> 

ባል ለሚስቱ የሚያስፈልጋትን የሚሰጥበት፣ ሚስትም ለባልዋ የሚያስፈልገውን የምትሰጥበት መልካም የሆነ የትዳር ሕይወት የሴሰኝነትን ኃጢአት ይከላከላል። ሰይጣን እንዳይፈትናችሁ ተከላከሉት ይላል ጳውሎስ። አለበለዚያ እነዚህ ሃሳቦች ወደአይምሮአችን ሊመጡና ሊፈትኑን ይችላሉ።

ግብረሰዶሞች በውስጣቸው ካለው ከዚህ ፍላጎት ነጻ መውጣት ይችላሉን? 1ኛ ቆሮ 6፣9-11

9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 11 ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።

የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ሕይወትን ለመኖር የሚያስችል ኃይል እንዳለ ይገልጽልናል። በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እነዚህ አማኞች በቀድሞ ኑሮአቸው ምን አይነት ሕይወት እንደነበራቸው ይገልጻል።

ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች >> … ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል!

ሃሌሉያ!

ጳውሎስ ለቲቶ በጻፈው ደብዳቤ የእግዚአብሔርን ቸርነት ከማየታችን በፊት <<ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥>> ነበርን ይላል። ከዚያም ጌታ አዳነን፤ እግዚአብሔር ይመስገን። ከሴሰኝነት ኃጢአት ከግብረሰዶምነትም እንዲሁ አዳነን። ከዚህ ሁሉ አዳነን። ጌታ ኢየሱስ ስለ ቅፍርናሆም ሲናገር ሰዶምና ገሞራ እናንተ የሰማችሁትን ቢሰሙ ኖሮ ንስሃ በገቡ ነበረ ይላል። ጌታ ኢየሱስ ንስሃ መግባት እንደሚያስፈልግ ይናገራል።

ጌታ ኢየሱስ ግብረሰዶምነትን በተመለከተ የሚለው ነገር ቢኖር ንስሃ መግባት እንደሚያስፈልግ ነው። ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነፁ ስለዚህም በዙፋኑ ፊት ይቆማሉ። የሚያነጻና የሚያጥብ አንድ ነገር አለ። ማንም ከሴሰኝነት ጋር መታገል አያስፈልገውም። ማንም <<እኔ እንደው በዚህ አካባቢ እቸገራለሁ>> ማለት አያስፈልገውም። ማንኛውም ሰው መፈታት ይችላል። መፈታትን የሚፈልግ ካለ መፈታትን ማግኘት ይቻላል።

ግብረሰዶማውያን ከዚህ ሰይጣናዊ ኃይል ነጻ መውጣት ይችላሉን?

አዎን ይችላሉ። በቆሮንቶስ የነበሩት ከነዚህ ከተፈጥሮ ውጪ ከሆኑ ነገሮች ነጻ መሆን ከቻሉ ማንኛውም ሰው ነጻ መሆን ይችላል። ሃዋርያው ጳውሎስ በሮሜና በቆሮንቶስ ላይ ስለግብረስጋ ጉዳይ የተመለከተውን ነገር ግልጽ አድርጎ ስለጻፈው እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

እነዚያ ሰዎች ከነዚህ ችግሮች ጋር የታገሉ ባይሆኑ እኛ ዛሬ ምንም ባላወቅን ነበር። የወንድ ለወንድ መጋባትን ልንባርከው አንችልም! እኛ ይሄንን ኃጢአት ያየነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን በእያንዳንዱን ትውልዱ ከዚህ ኃጢአት ሊያድን ሲሻ በታሪክ ውስጥ እናያለን።

እንግዲህ <<እንቀበለዋለን>> ልንል አንችልም። የተመሳሳይ ጾታዎችን ግንኙነት አንባርክም። ከዚህ ነገር ጋር ልንተባበር አንችልም። እነዚህን ሰዎች እጃችንን ጭነን <<እንባርካችኋለን>> ልንላቸው አንችልም። የእግዚአብሔርን ቁጣ በላያችን ላይ እናመጣለንና ይሄንን ልናደርግ ፈጽሞ አንችልም። ስለዚህ ይህ ነገር በጣም አስፈላጊ ነው።

<<ግብረሰዶምነት አብሮን የተፈጠረ ነገር ነውን?>> ለሚለው ጥያቄ የመጽሐፍ ቅዱስ መልስ <<አይደለም>> የሚል ነው!!

<<ይህ ነገር ክፉ መናፍስት በሰው ልጆች ላይ የሚያካሂዱት ስራ ውጤት ነውን>> ለሚለው ጥያቄ የመጽሐፍ ቅዱስ መልስ <<አዎን>> ነው። እንደዚህ እንደሆነም ልንረዳ ያስፈልገናል።

አሜን።

ይሄንን መዝሙር ዘመርን፤

<<አንድ የማውቀው ነገር ቢኖር ጸጋህ በቂ እንደሆነ ነው። የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ኃጢአቴንና በደሌን አሁን ይሸፍናል>>

 

መጋቢ ኦከ ግሪን ንግግራቸውን በመቀጠል…፤

ሰዎች በኃጢአታቸው ምክንያት ከጸጋ ውጪ ናቸው (እግዚአብሔር ሊምራቸው አይችልም) ብለን መቼም ቢሆን ማሰብ የለብንም። ጳውሎስ ሲናገር <<ከኃጢአተኞች ሁሉ ዋነኛ እኔ ነኝ>> ይላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ እንደበዛለት ይናገራል።

በ 1ኛ ቆሮ 6፤9-11 ደግሞ እነዚያን ሁሉ ኃጢአቶች ከዘረዘረ በኋላ ከነዚህ ሁሉና ከሴሰኝነትም መፈታት ይቻላል ይላል።

በሴሰኝነት ኃጢአት ባርነት ውስጥ የሚመላለሱ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው ነገር ቢኖር ከሁሉ የሚበልጠው የእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት ነው። ይህም ጸጋ አለ…ለሁላችንም ደግሞ ተሰጥቶአል።

ስለዚህም በዚህ ውስጥ የሚመላለሱትን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያለውን ጸጋ እንዲመለከቱ እናበረታታቸዋለን።

በሰዎች ልንፈርድባቸው አይገባንም…ጌታ ኢየሱስም ይሄንን አላደረገም። ነገር ግን ያገኛቸውን ሰዎች ሁሉ ባሉበት ሁኔታ ትልቅ አክብሮት ያሳያቸው ነበረ። ለምሳሌ በዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 8 ላይ ያገኛትን ኃጢአተኛ ሴት እንዲሁም በውሃው ጉድጓድ አጠገብ ያገኛትን ሴት መጥቀስ ይቻላል። ኢየሱስ ማንንም አያዋርድም። ምሕረትን (ጸጋን) ብቻ ይለግስ ነበረ። በኃጢአት ውስጥ የሚኖርን ማንንም ማዋረድ አይገባንም። ኃጢአትን አንታገስም ሰውየውን ግን እንታገሳለን።

ሰዎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ልናደርጋቸው የምንችለው ርህራሄና ምሕረት በማሳየት ነው። ቅዝቅዝ ያለ ነገር አሳይተን ማንንም ለጌታ አንማርክም።

ማንም ምክር ወይንም ጸሎት ከፈለገ ከስብሰባው በኋላ ሊያገኘኝ ይችላል። ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው ወደፊት ኑ ብዬ ግን ዛሬ ጥሪ አላቀርብም።

እስቲ አብረን እንጸልይ።

*******************************************************

 

መጋቢ ኦከ ግሪን