ቀን፤ 2005-10-30     

በኖቬምበር 9 2005 ስለተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ/የድጋፍ ሰልፍና (ማኒፌስቴሽን) እንዲሁም ስለግብረሰዶምነት እንቅስቃሴ በስዊድን የቀረበ ዘገባ/ገለጻ

 

  ዘገባውን በቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ
       
 

X

  የፍርድቤት ድርድሩን እዚህ ጋር ማዳመጥ  ትችላላችሁ
       
 

  የሰላማዊ/የድጋፍ ሰልፉን እዚህ ጋር ማየት ትችላላችሁ
       
 

  የመጋቢ ኦከ ግሪን ሙሉ መልእክት የአማርኛ  ትርጉም

ማውጫ

ዜናዎች

  1. መግቢያ
  2. ሰዶማዊነት በስዊድን (አጭር ታሪክ)
  3. የግብረሰዶምነት መንፈስና እንቅስቃሴዎች በስዊድን
  4. ቤተክርስቲያን ምን ማድረግ ትችላለች?
  5. የክርስትና እምነትና የሕይወት ዘይቤ አገር አቀፍ ማሕበር
  6. የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊድን ላሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ቀርቧል
  7. የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ የማስታወቂያ ፖስተር (በስዊድንኛ)
  8. ቀን፣ ቦታና ሰዓት እንዲሁም ፕሮግራም
  9. የግብረሰዶምን ኃጢአት እንጂ ግብረሰዶሞችን ወይንም ማንኛውንም ሰው ልንጠላ አልተጠራንም
  10. ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ

 

ዜናዎች

 

1.    መግቢያ

   በአካባቢያችን ምን እየተከናወነ እንደሆነ ማወቅና አውቀንም ለዚያ የሚገባውን ምላሽ መስጠት ከብዙ ነገር ሊጠብቀን ይችላል። (1ኛ ዜና 12፤32 እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።)

የሚከተሉትን ጥቅሶች ከእግዚአብሔር ቃል አንብበን እንጀምራለን

ሮሜ ምእራፍ አንድ፤

18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤

19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።

20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።

22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥

23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤

25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።

28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤

ዘሌዋውያን ምእራፍ አስራ ስምንት፤

     22. ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ጸያፍ ነገር ነውና።

 

ዘሌዋውያን ምእራፍ ሃያ፤

13፤ ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

 

   የእግዚአብሔር ቃል ሰዶማዊነትን በተመለከተ የሚለው ግልጽና የማያወላዳ ነገር ነው። እኛም የምንቆመው በዚህ በዘላለማዊው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ባለው እውነት መሰረት ነው።

    የግብረሰዶም መንፈስ ምን ምን አይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው? እንዴትስ ይሄንን ሂደት ማቆም/ማገድ እንችላለን? የሚለውን በአጭሩ እናነሳለን።

   የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ የምንወክል እንደመሆናችን በሕብረተሰብ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማድረግ መልካም ተጽእኖ ማምጣት እንችላለን

  •  ቤተክርስቲያን ለሚጠፋው አለም የእግዚአብሔር ትንቢታዊ ድምጽ ናት

 

2.    ሰዶማዊነት በስዊድን (አጭር ታሪክ)

   ግብረሰዶምነት 1864 ጀምሮ በስዊድን ወንጀል ነበረ። ስለዚህም ግብረሰዶም ሆኖ መገኘት የሚያስቀጣ  ነገር ነበረ!

    1944 ወንጀል መሆኑ ተሻረ።

    1988 ግብረሰዶሞች እንዲጋቡ በመንግስት ተፈቀደላቸው!

    2003 ግብረሰዶምነትን ተቃውሞ መናገር በሕግ ያስቀጣል የሚለው ሕግ ጸደቀ።

    በጁላኢ 2005 አርቲፊሻል ኢንሴሚኔሽን በተባለው ዘዴ ልጅ ማርገዝ ለሴትና ሴት (ለሌዝቢያኖች) ተፈቀደ።

  ዖክቶበር 27 ባለፈው ሐሙስ፣ የስዊድን ሉተራን ቤተክርስቲያነ ግብረሰዶሞችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ጋብቻን በመሰለ ስርዓት ለመባረክ በከፍተኛ ድምጽ አጸደቀች።

 

3.    የግብረሰዶምነት መንፈስና እንቅስቃሴዎች በስዊድን 

  • ግብረሰዶሞች በቴሌቪዥን ትልቅ ስፍራ እያገኙ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት መጋባት ምንም የለውም እያሉ በድፍረት እየነዙ ይገኛሉ። ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ ግን ወይ በማስ ሚዲያ አይጋበዝም፣ ወይ በፍርሃትና በሌላም ምክንያትእግዚአብሔር ቃል በድፍረት ሲቆም አይታይም።

  • ግብረሰዶሞች ከመንግስት ብዙ ሚሊዮን ክሮነር ተቆራጭ እየተደረገላቸው በየትምሕርት ቤቱ  ግብረ ሰዶምነት  ምንም ከተፈጥሮ ውጭ ያይደለ (ኖርማል) ነገር እንደሆነ በማስተማር ንቃተ ሕሊና ይሰጣሉ። ይሄ ሁሉ በመንግስት በጎ ፈቃድና አበረታችነት ይደረጋል።

  • የስዊድን ሉተራዊት ቤተክርስቲያን (ስቬንስካ ሺርካን) ሃሙስ 2005-10-27 ለግብረሰዶሞች የባልና ሚስትነት አይነት ቡራኬ ለመስጠት  በከፍተኛ ድምጽ ብልጫ አጽድቆአል። ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭም ነገር ነው!

  • ግብረሰዶምነትን በስዊድን ለማስፋፋትና የሕብረተሰብን አስተያየት ለመቀየር (ኦፒኒዮን ቢልድኒንግ ለሚባለው) በማስ ሚዲያና በትምሕርት ቤት ወ.ዘ.ተ. በመንግስት ከፍተኛ ማበረታታትና እረዳታ፣ ድጋፍም እየተሰጣቸው ቀለብም እየተቆረጠላቸው ይገኛል።

  • ግብረሰዶምነት ኃጢአት ነው! የእግዚአብሔርን ቅጣትና እርግማን ያመጣል! የሚለውን መልእክት ለመናገር ግን ብዙ ቤተክርስቲያኖችና መጋቢዎች ድፍረት ሲያጡ ይስተዋላል።

  • ግብረሰዶሞች እንደሕዝብ ክፍል (ፎልክግሩፕ) ተቆጥረው እነርሱን የሚያስጠላ ወይንም ለእነርሱ አክብሮት የሚነሳ ነገር መናገር እንዲያስከስስ ተደርጎ የስዊድን ሕግ (ሄትስ ላገን) ተቀይሯል!

  • ይህ ህግ ከምእራቡ ሕብረተሰብ በጣም በጥቂት አገሮች የሚገኝ ሕግ ሲሆን ስዊድን ይሄንን ካጸደቁት ጥቂት አገሮች አንዷ ናት።

  • በሌሎች አገሮች እንዲህ የግብረሰዶም መንፈስ ሊስፋፋ ካልቻለባቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ

  • ጠንካራና የምትጸልይና ተጽእኖም የምታደርት ቤተክርስቲያን ስላለችና

  • አገልጋዮች በታላቅ ድፍረት ይሄንን ርኩሰት ስለሚቃወሙ ነው (ለዚህም የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ እጅግ ተስፋፍቶ የሚገኝበትን አሜሪካን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል)

  • ክርስቲያኖች በሕብረተሰብ ላይና በፖለቲካው ስርዓት ላይ ሳይቀር ጫና ማድረግ በቻሉባቸው አገሮች ይሄንን አጀንዳቸውን ማረመድ አልቻሉም

  • በስዊድን ያሉ ቤተክርስቲያኖች ግን በዚህ ነገር እስካሁን ያሳዩት እርምጃ እጅግ አነስተኛ ነው!!! 

  • የእኛ ቤተክርስቲያን ግን ከዚህ መንፈስ ጋር የማትተባበር መሆንዋን በግልጽ አቋም ወስዳ ለማሳየት መርጣለች! እግዚአብሔር ይመስገን!

  • ይሄ ሂደት የከነከናቸውና እግዚአብሔርም በዚህ ነገር መልእክት ለስዊድን ሰጥቶኛል የሚሉ አንድ የፔንቴኮስታል ቤተክርስቲያን መጋቢ (መጋቢ ኦከ ግሪን) ቦርይሆልም በምትገኘው ቤተክርስቲያናቸው በጁላይ 2003 .. ስለግብረሰዶም ምንነት አንድ መልእክት አቀረቡ።

  • ኦከ ግሪን በስብከታቸው እኛን ነክተዋል አክብሮት አላሳዩንም ብለው የግብረሰዶም እንቅስቃሴ አራማጆች ከሰሷቸው!

 

መጋቢ ኦከ ግሪን

  • የስዊድን የመጀመሪያ ፍርድቤት (ቲንግስሬተን) ዲሞክራሲያዊ ነን በሚሉ በምእራባውያን አገሮች ታሪክ ተደርጎ የማይታወቀውን አዲስ ፍርድ በማስተላለፍ የአንድ ወር እስራት ፈረደባቸው።

  • ይህ ሁኔታ ብዙዎችን ሊያሳዝንና ሊያስቆጣ ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ በአንድነት እንዲነሳ ሊያደርግ ሲገባው በምትኩ እኚህን ሰው እንደሊቬትስ ኡርድ ካሉ ከጥቂት ቤተ ክርስቲያኖች በቀር አብሮአቸው የቆመና ያበረታታቸው የለም።

  • የእኛ ቤተክርስቲያን ግን በቀጥታ እኚህን አገልጋይ ስልክ ደውሎ በማግኘትና በማበረታታት በጸሎትም እንደምናስባቸው በመግለጽ አበረታታቸዋለች።

  • ከዚያም ኦከ ግሪን ይግባኝ ብለው ወደበላይ ፍርድ ቤት አመልከተው ጉዳያቸው ታይቶ በዚህ አመት መጀመሪያ ሆቭ ሬት የተባለው የበላይ ፍርድ ቤት የቲንግስ ሬትን ፍርድ ገልብጦ በነጻ ለቆአቸዋል

  • ሆኖም አቃቢ ሕጉ ጉዳዩን ለከፍተኛፍ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለቱ በፊታችን ኖቬምበር 9 / 2005 የስዊድን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይሄንን ጉዳይ ይመለከተዋል!

  • ግብረሰዶሞች ተቀባይነት ለማግኘት የሚጠቀሙት አንድ ትልቅ መሳሪያ እራሳቸውን እንደተጠቂና እንደተጎጂ አድርጎ ማቅረብ ነው። ከዚህ በተረፈ ደፈር ብለው የሚናገሩ ሰዎችን በማጥቃት ሌሎችም ፈርተው ምንም እርምጃ እንዳይወስዱ ለማድረግ ይጥራሉ!

 

4.    ቤተክርስቲያን ምን ማድረግ ትችላለች?

  • በምልጃ የእግዚአብሔርን ፊት ልትፈልግና የእግዚአብሔርን ምሕረት ለዚህ ምድር ልትለምን ያስፈልጋል! (ኤር 297

  • እግዚብሔር ለቤተክርስቲያን በሰጣት ልዩ ስልጣን በጸሎት በመንፈሳዊ የእምነት ጦርነት  የክፋት መንፈሳዊ ሃይላትንና ሃይለኛውን  ማሰር  ይሄንንም ሂደት በመንፈስ ማገድ ትችላለች!!! (ውጊያችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና!  ማቴ 1818  እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።)

  • ሰዎች ከዚህ ርኩሰት ወጥተው ነጻ እንዲወጡ እያስተማረች ሰይጣን የሚነዛውን ውሸት በማጋለጥ ሰዎችን ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቃ ማውጣት ትችላለች (2 ቆሮ 103-6 ይሁዳ 22-23)

  • በቤተክርስቲያን ደረጃ በሕብረተሰብ ውስጥ አቋሟን ግልጽ በማድረግ ከክፋትና ከእርኩሰት ጋር እንደማትተባበርም በመስታወቅ ታላቅ የሕሊና ድምጽ መሆን ትችላለች  (1ጴጥ 212 ማቴ 144)

  • ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በግለሰብና በቤተክርስቲያን ደረጃ ማሕበራዊና እንዲሁም ፖለቲካዊ ተጽእኖን በሕብረተሰብ ላይ ማምጣት ትችላለች! (ሐዋ 67)

  • የስዊድን የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተቋቋመው ሌቪ ጴጥሮስ በተባሉ የጰንጠቆስጤ ቤተክርስቲያን ዋና መሪ ነበረ

  • ከብዙ አመት የማያሰልስ ጥረት በኋላ ይህ ፓርቲ ፓርላማ ገብቶ በመንግስት ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ማድረግ ጀመረ

  • ዛሬ ግን ይሄው ፓርቲ ግብረሰዶሞችን ሲያስተናግድ ይታያል

  • ይህ ሂደት እንዲለወጥ የሚሹ ብዙ ክርስቲያኖች በስዊድን እነዳሉ ግን እናውቃለን። ከእነዚህም አንዱ አር...ኤል. የተባለው የክርስቲያን ሎቢ እንቅስቃሴ መስራች የሆነው ስቴፋን ግሬቭለ ይገኝበታል።

 

5.    የክርስትና እምነትና የሕይወት ዘይቤ አገር አቀፍ ማሕበር

ይህ ወንጌላዊ ወንድም እየተከናወነ ያለው ሂደት መልካም ወዳልሆነ አቅጣጫ እየሄደ እንዳለ ተመልክቶ አገር አቀፍ የክርስትና እምነትና የሕይወት ዘይቤ ማሕበር (አር. ኬ. ቲ. ኤል) የሚባል የክርስቲያን ሎቢ እንቅስቃሴ መስርቷል። በዚህም አገልግሎት በቴሌቪዥን ከግብረሰዶም አራማጆች ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ የቃል ምልልስ ላይ መካፈል ጀምሯል።  ባለፈው ጁላይ በቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ የሰጠውን ቃለ ምልልስ በስዊድንኛ እዚህ ጋር ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ይሄው በዚህ ወንድም የተመሰረተው የክርስቲያን ማሕበር መጋቢ ኦከ ግሪን በተከሰሱበት በኖቬምበር 9 እለት ሰላማዊ ሰልፍ/የድጋፍ ሰልፍና የሕዝብን አስተሳሰብ የመቀየር ስብሰባ (ኦፒኒየን ሚቲንግ) አዘጋጅቷል። ለዚህም ብዙ ቤተክርስቲያኖች ታድመዋል። ይሄንን ጥሪ ከዚህ በታች ማንበብ ትችላላችሁ።

ስለዚህ ሰውና ስለአገልግሎቱ ስለጀመረውም ማሕበር አላማ በድረ ገጾቻቸው ላይ ማግኘት ይቻላል። ድረ ገጹ እነሆ። (በስዊድንኛ ነው)

5 ödesfrågor för Sverige
Stefan G
e-post: stefan@rktl.se
telefon: 076- 8015703

 

 

6.    የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በስዊድን ላሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ቀርቧል

Bäste Präst/Pastor/Förkunnare

ውድ ቄስ/መጋቢ/አገልጋይ

 

Den 9 november ställs er kollega och broder Åke Green inför rätta i Högsta Domstolen efter sin numera välkända predikan. Många journalister, advokater, pastorer/predikanter och medborgare anser att en fällande dom klart strider mot lagen om yttrandefrihet och det finns en stor vanmakt och oro över den här utvecklingen.

ኖቬምበር 9 የእናንተው ወንድምና ባልንጀራ ኦከ ግሪን ዝነኛ በሆነው ስብከቱ ምክንያት በከፍተኛው ፍርድቤት  ፊት ይቆማል። ብዙ ጋዜጠኞች፣ ጠበቆች፣ መጋቢዎች/አግልጋዮች እንዲሁም ዜጎች በኦከ ግሪን ላይ ፍርድቤቱ ቢፈርድባቸው  ከሃይማኖትና ሃሳብን