.
ዋናው ገጽ > ሌሎች አስፈላጊ ገጾች > ቆም የሚያደርጉ ጥቅሶች > 2017-03-27 "...እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት..."

2017-03-27 "...እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት..."

ትንቢተ ኢሳይያስ 55

1 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።

2 ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።

3 ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፤ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።

4 እነሆ፥ ለአሕዛብ ምስክር፥ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።

5 እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ።

6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤

7 ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።

8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡

9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥

11 ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።

12 እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።

13 በእሾህም ፋንታ ጥድ በኩርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያን ለዘላለምም የማይጠፋ፥ ምልክት ይሆናል።


ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ አምስት ሰዓት ተኩል (11፡30) የታዳጊ ወጣቶች የአምልኮ ጊዜ በስዊድንኛ
  7. ዘውትር እሁድ ከአምስት ሰዓት (10፡30) እስከ ስድስት ሰዓት (11፡30) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  8. እሁድ ከከአራት እስከ ስድስት ሰዓት (10፡00-12:30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረናል

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::

ክፍል ለማስያዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይደውሉ:

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ