.
ዋናው ገጽ > ሌሎች አስፈላጊ ገጾች > ቆም የሚያደርጉ ጥቅሶች > 2017-04-30 "...በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ...አልበደለም፥ ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠም"

2017-04-30 "...በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ...አልበደለም፥ ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠም"

ኢዮብ ም.1
20  ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤ 21  እንዲህም አለ፦ ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን። 22  በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠምመጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 12
15  ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር። 16  ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ዳዊትም ጾመ፥ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ። 17  የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፥ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም። 18  በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳዊትም ባሪያዎች፦ ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፤ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን? በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ። 19  ዳዊትም ባሪያዎቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ አወቀ ዳዊትም ባሪያዎቹን፦ ሕፃኑ ሞቶአል? አላቸው። እነርሱም፦ ሞቶአል አሉት። 20  ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ። እንጀራ አምጡልኝ አለ በፊቱም አቀረቡለት፥ በላም። 21  ባሪያዎቹም፦ ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድር ነው? በሕይወት ሳለ ስለ ሕፃኑ ጾምህና አለቀስህ፤ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ አሉት። 22  እርሱም፦ ሕፃኑ ሕያው ሳለ፦ እግዚአብሔር ይምረኝ፥ ሕፃኑም በሕይወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ብዬ ጾምሁ አለቅሰሁም። 23  አሁን ግን ሞቶአል፤ የምጾመው ስለ ምንድር ነው? በውኑ እንግዲህ እመልሰው ዘንድ ይቻለኛልን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም አለ። 24  ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፥ ወደ እርስዋም ገባ፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፥ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው፤ 25  ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው።



ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ አምስት ሰዓት ተኩል (11፡30) የታዳጊ ወጣቶች የአምልኮ ጊዜ በስዊድንኛ
  7. ዘውትር እሁድ ከአምስት ሰዓት (10፡30) እስከ ስድስት ሰዓት (11፡30) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  8. እሁድ ከከአራት እስከ ስድስት ሰዓት (10፡00-12:30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረናል

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::

ክፍል ለማስያዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይደውሉ:

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ