.
ዋናው ገጽ > ሌሎች አስፈላጊ ገጾች > ቆም የሚያደርጉ ጥቅሶች > 2017-11-23 "...ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ..."

2017-11-23 "...ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ..."

"ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ።" (ሐዋ. 26:20)

"እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። (ሐዋ. 3:19-20)

"ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ" (ሐዋ. 11:18 )

"ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?" (ሮሜ ሰዎች 2:4)

"ደግሞም፦ ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:25-26)

"እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።" (የዮሐንስ ራእይ 2:5)


ቋንቋ ምረጥ

ተጨማሪ ድረ ገጾች

ማስታወቂያዎች

መደበኛ (የዘወትር) ፕሮግራሞቻችን፤


  1. መጋቢዎቻችንን በሚከተለው ቁጥር ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ መጋቢ ንጉሱ ጉሌ (+46 (0)735115951) መጋቢ ወሰን ተሾመ (+46 (0)736162913)

  2. ሰኞ 10:00-14:00 የምክር አገልግሎት በወንድም ሙሴ ሃይሉ (በስልክ ቁ. 0707568264) በመደወል ልታገኙት ትችላላችሁ።
  3. ዘወትር ረቡዕ ከጥዋቱ አራት ሰዓት (10፡00) እስከ አስር ሰዓት (15፡00) የጾምና የጸሎት ጊዜ አለን
  4. ሀሙስ 18:00—20:00 የመጽሓፍ ቅዱሰ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳል:: እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ አንድ የጥናት ቡድን ይኖራል
  5. በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ18፡00 ሰዓት እስከ 20፡00 ሰዓት የምሽት ፀሎት ጊዜ አለን።
  6. ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት (10፡00) እስከ አምስት ሰዓት ተኩል (11፡30) የታዳጊ ወጣቶች የአምልኮ ጊዜ በስዊድንኛ
  7. ዘውትር እሁድ ከአምስት ሰዓት (10፡30) እስከ ስድስት ሰዓት (11፡30) ድረስ የጸሎት ጊዜና
  8. እሁድ ከከአራት እስከ ስድስት ሰዓት (10፡00-12:30) ድረስ የአምልኮ ጊዜ ይኖረናል

  • ከ3 እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች የሰንበት ትምሕርት ይሰጣቸዋል
  • ከ13 እስከ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችን በየእሁዱ እናስተምራለን::

ክፍል ለማስያዝ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይደውሉ:

የኢ. ወ. ቤ/ክ ሶሻል ሚድያ